ጉዞ ጉራጌ ፌስቲቫል እና ቫኬሽን ፕሮግራም
ጉራጌን በ ኢንቨስትመንት የማነቃቃት አላማ ያለው
የጉራጌን ቱሪዝም የማነቃቃት አላማ ያለው "ጉዞ ጉራጌ 3 " በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ አስራ አምስት ቀናት ቀርተውታል። ይህ ጉዞ ከእስከአሁኑ በተለየ መልኩ ሙሉ ለሙሉ የክብር እንግዶችን ብቻ በመያዝ ወደ ጊቤ ፓርክና አካባቢው የሚደረግ ጉብኝት ና ካምፒንግ ነው።
አዳዲስ ነገሮች እንሞክራለን ካምፒንግ አርጎ በደን መሀል ክትፎ እንበላለን። ክትፎ ጫካ ልትገባ ነው😂 ከተፈጥሮ ሀብት አልፈንም የጉራጌ ህፃናት እየተማሩባቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችን ና እናቶች ቀድተው የሚጠጧቸውን ወንዞች እናያለን። የጉራጌ ሁለት መልኮች 🤔
የጉዞ ጉራጌ ተጨማሪ ስራዎች
ቱባ ባህል ወዳለበት ጉራጌ ለመሄድ እየፈለጉ የሚወስደኝ ሰው አጣሁ ብሎ መማረር ቀረ።
ከወር በፊት የማይረሳ ጉዞ ወደ ጉራጌ ያደረገው ጉዞ ጉራጌ አሁንም በመስቀል ወደ ጉንችሬ ያመራል። ከመስከረም 15 እስከ መስከረም 17 ከጎመን ክትፎ ጀምረን እስከ ሻኛ ድረስ ሁሉንም ባህል አብረን እንታደማለን።
ክትፎ ለመጠጣት ዝግጁ ናችሁ ?
ጥሬ ስጋ ፣ ክትፎ ፣ ጎመን ክትፎ ፣ ዝማሞጃት ...አንድም የሚቀር የለም።
ባህላዊ ደመራን በጀፎረ መንፈሳዊውን ደመራ በቅዱስ ዮሀንስ ቤተክርስትያን ታድመን። በአዛውንቶች ስኬት በስኬት የሚያደርግ ምርቃት ተመርቀን አመቱን በደስታ እንጀምረዋለን።
ለሚስኪኖች መድረስ ከሚስኪኖች ማዕድ መጋራት
በ "ጉዞ ጉራጌ" የተለያዩ እንግዶች ጋዜጠኞችንና የቱሪዝም ባለሙያዎችን በግብዣ ...10 ተጓዦችን ደግሞ በክፍያ ወደ ጉንችሬ ወስደን በዓሉን ደስ በሚል ሁኔታ አሳልፈናል። ሁሌም ጉዞዎች ሲዘጋጁ በነዋሪው ህዝብ ላይ ድሎትንና መዝናናትን ከማሣየት ባሻገር ነዋሪውንም ማገዝና ማሣተፍ ግድ ነው ብለን ስለምናምን የጉዞው ማጠናቀቂያ አቅም ለሌላቸው ሀያ ቤተሰቦች በሬ ለብቻቸው ገዝተን በክብር ማቀራጨት ነው።
ለዚህም እስከ አሁን ድረስ ከእኛም ከእናንተም 40 ሺ 300 ብር ማሠባሠብ ችለናል። የነገ አላማችን እንዲሳካ ዛሬ ባየነው ገበያ 55 ሺ ብር ገደማ ያስፈልገናልና የቀረንን 15 ሺ ብር ለመሸፈን 150 ሰዎች መቶ መቶ ብር እንድታግዙን እንጠይቃለን።
ዘንድሮ በሚዲያ የጀመርነው ስራ ቀጣይ አመት ተስፋፍቶ ወደ ጉራጌ ሀገር የመስቀል የቱሪዝም ጉዞዎች በየሰፈሩ አንዳንድ ወይፈን ለተቸገሩ ሰዎች የሚገዛበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ተስፋ እናደርጋለን። በተለይም ዘንድሮ ለአረፋ ባዘጋጀነው የአረጋውያን እገዛ ቻሌንጅ በብዛት የተሣተፉት ክርስትያኖች አሁን ለመስቀል እያዘጋጀን ባለነው ቻሌንጅ ደግሞ አብዛኛው ተሣታፊዎች ሙስሊም ቤተሰቦቻችን መሆናቸው አስደስቶናል። ተጠናክሮ እንዲቀጥል የምንፈልገውም ይሄን ህብረትና አንድነት ነው።
በቀሩት ሰአታት 150 ሰዎች ፈልገናል አለሁ በሉን 🙏